I'm New
ለእንግዶች

Fulness of Christ church is a place where people can meet Jesus,  engage in life-giving community, and everyone is welcome. We believe in creating a space where people can have authentic encounters with Christ, discover their gifts and use them for God's glory. Join us for our Sunday services!
የክርስቶስ ሙላት ቤተክርስቲያን ሰዎች ከህይወታቸው ቤዛ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚገናኙበት፣ ህይወት ሰጭ በሆኑ ማህበራዊ ትስስሮች ውስጥ የሚገቡበት ስለሆነ እንኳን ደህና መጡ፡፡ ሰዎች ከጌታ ጋር ልዩ የሆነ ግንኙነት ውስጥ ገብተው በህይወታቸው ያለውን ወሳኝ የእግዚአብሄር ጥሪ አውቀው ለእግዚአብሄር ክብር እንዲጠቀሙበት የሚያደርግ ሁኔታ በእግዚአብሄር መንፈስ እገዛና በቃሉ መሰረት እንፈጥራለን፡፡ በየዕሁዱ በሚኖረን የአምልኮ ፕሮግራማችን ላይ ተገኝተው አብረውን ይካፈሉ፡፡

When we Meet
የፕሮግራሞቻችን ቀናቶች

Sunday Mornings
ዕሁድ ጠዋት

10:00 AM

Wednesday evening
ዕሮብ ማታ

5:30pm

What To Expect
በፕሮግራሞቻችን ሰዓት

A typical service will last about 2 hours. We sing a good mix of contemporary and traditional music that is led by our worship team. There is childcare available and activities for all age groups. Plan to hang around after the service for fellowship and meeting new people.
ፕሮግራሞቻችን ቢበዛ ለ2 ሰዓታት ያክል ነው የሚቆዩት፡፡ ከድሮዎቹም ሆነ ከአሁኖቹ የተለያዩ የሰማዩን አምላክ በምድር ማምለክ የምንችልባቸውን ዝማሬዎች እንዘምራለን፡፡ ይህም የሚሆነው እግዚአብሄር ቀብቶ ባስነሳልን የአምልኮ መሪዎቻችን ይሆናል፡፡ በቤተክርስቲያኒቱ መጋቢና እንዲሁም በዙሪያው እግዚአብሄር ባስነሳቸው የህያው አምላክ አገልጋዮች ስርነቀል ሰማያዊውን መረዳት በምድር የሚያጎናጽፈን የእግዚአብሄር ቃል ትምህርት ይሰጣል፡፡ የተለያየ ዕድሜ ላላቸው ልጆችና ህጻናት የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትና የተለያዩ እንቅስቃሴዎች አሉን፡፡ ከፕሮግራም በኋላም ከሰዎች ጋር የሚተዋወቁበትና ህብረት የሚያደርጉበት የሻይና ቡና ጊዜ ስለሚኖረን ይህን ታሳቢ አድርገው ትንሽ ለመቆየት አቅደው ይምጡ፡፡

How To Contact Us
ከኛ ጋር ለመገናኘት

We'd love to hear from you. Fill out the form below to get started

ያላችሁን ሃሳብ ብታጋሩን ደስ ይለናል
ለመጀመሪያ እንዲሆነን ከታች ያለውን ፎርም ይሙሉ