Leadership

Pastors & Staff

Fisseha tesfaye

lead Pastor

Pastor, Fisseha Tesfaye, who is a Jesus-following, mission-leading, church-serving, people-loving, Bible-preaching pastor. He’s grateful to be a nobody trying to tell everybody about Somebody.
Born in Dembi Dollo, Oromia, Ethiopia, Pastor Fisseha grew up as the son of a successful business man in Dembidollo. Pastor Fisseha had started his professional career as a civil engineer before he gets in to full time ministry in Ethiopian Full Gospel Church. He started Fullness of Christ church in February 2018 in Alexandria Virginia. He is married to his wife Wedajie Tariku. They both were blessed with 4 children, 3 girls and a boy. Mezmure Tesfaye (Mechanical engineer) Endegena Tesfaye, Hiriya tesfaye, and Siinta'e Tesfaye.
መጋቢ ፍሰሐ ተስፋዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ፣ የተልዕኮ መሪ፣ የቤተክርስቲያን አገልጋይ፣ የሰዎች ወዳጅ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ሰባኪ ነው፡፡ ጉልህ ስፍራ ያለውን ጌታ ለሰዎች ሁሉ ለመንገር እራሱ ግን ምንም ሆኖ ባለመገኘቱ ክብር ይሰማዋል፡፡
ከአንድ ስኬታማ የንግድ ተቋም ባለቤት ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሚያ ክልል በደምቢዶሎ ከተማ ተወልዶ ያደገና እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እስኪጨርስ ድረስ እዚያው የኖረ ነው፡፡ መጋቢ ፍሰሐ የምህንድስና ሙያ ባለቤት የነበረ ሲሆን በኢ.ዘ.አ በ1980 ዓ.ም ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኙ የተቀበለና በሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የሙሉ ጊዜ አገልግሎቱን ከመጀመሩ አስቀድሞ በተለያዩ የመንግስትና የግል መስራ ቤቶች በዚሁ ሙያ ሲሰራ የቆየ ነበር፡፡
ፓስተር ፍሰሐ ከደምቢዶሎ ሙሉ ወንጌል እንዲሁም በዙሪያው ባሉ ከተሞች ከዚያም በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በመዘዋወር የእግዚአብሄርን ስራ ሲሰራ የቆየ ሲሆን በፈርንጆቹ አቆጣጠር በ2009 ከእግዚአብሄር በተቀበለው ራዕይ መሰረት ከቤተሰቡ ጋር ኑሮውን አሜሪካን አገር ለማድረግ ወደ ፔንሲልቬኒያ ግዛት አቅንቷል፡፡
በዚሁ በፔንሲልቬኒያ ግዛት በላንካስተር ከተማ ከAssembly of God church ጋር በመሆን አዲስ ህይወት ቤተክርስቲያንን አቋቁሞ ከዚያ በ2015 ኑሮውን በቨርጂኒያ ግዛት አሌክዛንድሪያ ከተማ በማድረግ በ2018 የክርስቶስ ሙላት ቤተክርስቲያንን ከቤተሰቡ ጋር በሚኖርባት አፓርታማ ውስጥ ጀመረ፡፡ የክርስቶስ ሙላት ቤተክርስቲያንም ለብዙ ቤተክርስቲያናት መከፈት ትልቅ ድርሻ እንዲኖራት በጌታ ጸጋ አስችሏል፡፡
መጋቢ ፍሰሐ ተስፋዬ ክዳጄ ታሪኩ ጋር ባለትዳርና የአራት (3 ሴቶችና 1 ወንድ) ልጆች አባት ነው፡፡    
E-mail: fisseha@fullnessofchrist.org
Tel. 5714149212

Pastor Afework Tesfaye

Associate Pastor

Pastor Afework Tesfaye is a born-again Jesus loving family man dedicated to the ministry of God for the advancement of his kingdom. He is one of the leaders of Fullness of Christ church. He lives and serves with his wife Bety and his 2 lovely children Anasimos and Efrata.
ፓስተር ፈወርቅ ተስፋዬ ዳግም የተወለደ ጌታን የሚወድ የእግዚአብሄር መንግስት ይሰፋ ዘንድ  ራሱን ለጌታ አምልኮና ለአገልግሎት የሰጠ አገልጋይ ወንድም ነው፡፡ ከተወደደችው ባለቤቱና ከተወደዱ ሁለት ልጆች አናሲሞስና ኤፍራታ ጋር በአሌክዛንደሪያ የሚኖርና ከክርስቶስ ሙላት ቤተክርስቲያን መሪዎች አንዱ ነው፡፡

Yiftusira Gebregziabher

Treasurer & Youth ministry leader

Yoftusira is one of the team member when Fullness of Christ church was founded. Her commitment to Christ and faithful commitment to the ministry she endeavors is quite exemplary. She serves as our church's treasurer and takes car of the financial accounting and communications. On top of that she is one of the leaders in the youth ministry and takes part in the leading of the worship.
እህታችን ይፍቱስራ እኛ በምንጠራት ስሟ ቹቹ የክርስቶስ ሙላት ቤተክርስቲያንን ከጀመሩት የመጀመሪያዎች መካከል አንዷ ናት፡፡ ቹቹ ለጌታ ያለት ፍቅርና ለተሰጣት ኃላፊነት ያላት መሰጠትና ታማኝነት ለሁሉም ሰው ምሳሌ እንድትሆን አድረጓታል፡፡ በቤተክርስቲያናችን በገንዘብ ያዥነትና ይህንኑ በተመለከተ ማንኛውንም የሂሳብ ስራና ከሚመለከታቸው ጋር ግንኙነት የምታደርገው እሷ ናት፡፡
ቹቹ ከዚህም በተጨማሪ የቤተክርስቲያኒቱን የወጣቶች አገልግሎት የምትመራ እንዲሁም የአምልኮ ቡድን አባል በመሆንም ጭምር ታገለግላለች፡፡

Endegena Tesfaye

Worship Leader

ዘማሪት እንደገና ፍሰሐ ተስፋዬ የቤተክርስቲያኒቱ ዋና መጋቢ ሁለተኛ ልጅ ስትሆን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ በአምሎኮ መሪነት ከሌሎች ጋር አብራ የምታገለግል ነች፡፡ እንደገና ገና ከህጻንነቷ ጀምሮ ባደረባት የመዘመርና እግዚአብሄርን በዝማሬ የማምለክ ከፍተኛ ፍላጎትን ጸጋ ዛሬ ላይ ጎልቶ እየታየባት ጌታን በማምለክ ሌሎቻችንም በልዩ ሁኔታ እንድናመለክ እያገዘችን ያለች እግዚአብሄር በመካከላችን ያስነሳት የእግዚአብሄር አገልጋይ ናት፡፡

Belay adere

Deacon

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Vestibulum faucibus accumsan nulla, non faucibus velit convallis et. Nulla tempus placerat massa. 

Zufan Gidey

Children ministry

Zufan Gidey is a mother of three and has a heart for the children. She leads the children's Sunday school and organize the ministry with her groups.